የአማርኛ የራድዮ መርሃግብር - ከጥቅምት 2009 እስከ መጋቢት 2009 ዓም | |||||||
---|---|---|---|---|---|---|---|
ሰኞ | ማክሰኞ | ረቡዕ | ሐሙስ | ዓርብ | ቅዳሜ | እሁድ | |
16:00 UTC |
የዓለም ዜና፣ዝግጅቱ በተለይ ከኢትዮጵያ፣ ከአፍሪቃ እና ከመላው ዓለም ስለተገኙ መረጃዎች በየቀኑ የአሥር ደቂቃ አዲስ ዜና ይቀርብበታል። |
||||||
16:10 UTC |
የዜና መጽሔት፣የዕለቱ ዓበይት ጉዳዮች የሚተነተንበት ከሰኞ እስከ ዓርብ የሚተላለፍ ዝግጅት ነው። |
የአድማጮች ማህደር፣ይኸው ሳምንታዊ ዝግጅት አድማጮች የሚልኩዋቸው አስተያየቶች፣ ጥያቄዎች እና ግጥሞች የሚስተናገድበት መድረክ ነው። |
እንወያይ፣ኢትዮጵያን በሚመለከቱ አርዕስት ላይ ከተለያዩ እንግዶች እና በተለያዩት አገሮች ከሚገኙት ወኪሎቻችን ጋር የሚካሄድ ሳምንታዊ የውይይት ዝግጅት ነው። |
||||
16:30 UTC |
ማህደረ ዜና፣በሳምንቱ ውስጥ የተከናወነ ወይም የሚከናወን አንድ ዓቢይ ፖለቲካዊ ጉዳይን ያስተነትናል። |
ጤና እና አካባቢ፣ሳምንታዊው ዝግጅት በኢትዮጵያ፣ በአፍሪቃ እና በመላው ዓለም የተፈጥሮ አካባቢ ሁኔታ፣ የአየር ፀባይ ለውጥ ተፅዕኖ፣ በጤና እና በሴቶች ሁኔታ ላይ ያተኮሩ ጉዳዮች ይቃኙበታል። |
ከኤኮኖሚው ዓለም፣ለዓለም፣ በተለይ፣ ለኢትዮጵያ ኤኮኖሚያዊ ሂደቶች ትኩረት የሚሰጥ ዝግጅት ነው። |
የባህል መድረክ፣በተለይ የኢትዮጵያውያን የኪነ ጥበብ ስራዎችን፣ እንዲሁም፣ በጀርመን/አውሮጳ እና በሌሎች ባህሎች መካከል የሚደረገውን ግንኙነት የሚያስቃኝ ሳምንታዊ ዝግጅት ነው። |
የወጣቶች ዓለም፣ወጣት ኢትዮጵያውያንን የሚመለከቱ እና የሚያዝናኑ አርዕስትን እያነሳ ከሚመለከታቸው ጋር በሚደረግ ውይይት የሚጠናቀር ሳምንታዊ ዝግጅት ነው። |
ትኩረት በአፍሪቃ፣በአፍሪቃ ስለተከናወኑ ወይም ስለሚከናወኑ ዓበይት ወቅታዊ ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ዘገባዎች እና ትንታኔዎች የሚዳሰስበት፣ እንዲሁም፣ የጋዜጦች አስተያየት የሚታይበት ሳምንታዊ ዝግጅት ነው። |
|
16:43 UTC |
ስፖርት፣በኢትዮጵያ ፣ በአውሮጳ/በዓለም የተካሄዱ የስፖርት ክንውኖችን የሚያስቃኝ ሳምንታዊ ዝግጅት ነው። |
አውሮጳ እና ጀርመን፣የአህጉሩ ዓበይት ርዕሶችን፣ በጀርመን እና በሌሎች የአውሮጳ ሀገራት የሚኖሩ ባለሙያ ኢትዮጵያውያንን ስራ ይዳስሳል። |
ሳይንስ እና ህብረተሰብ፣ሳምንታዊው ዝግጅት ሳይንሳዊ እና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን እና ለህብረተሰቡ የያዙትን ጠቀሜታ ይመለከታል። |
የማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ቅኝትየማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች የሳምንቱ አብይ መነጋገሪያ ጉዳይ ይተነተንበታል። ንቁ ተሳታፊዎችም ይቀርቡበታል። |
መዝናኛ፣በሙዚቃው፣ በትያትር፣ ባጠቃላይ በኪነቱ ዘርፍ ከተሰማሩ አርቲስቶች እና ባከናወኑት ስራ ዝና ካገኙ ግለሰቦች ጋር ጭውውት የሚደረግበት ዝግጅት ነው። |
||
16:55 UTC |
የማጠቃለያ ዜናየዕለቱ ዓበይት ዜና በአጭሩ የሚቀርብበት ዝግጅት ነው። |